አራተኛው የትዊተር ዘመቻ

ኢትዮጵያውያን አገር ወዳዶች አራተኛውን የትዊተር ዘመቻቸው ፌብሩዋሪ 7 ቀን ለማድረግ ወስነዋል።ይህ ጥረት ከዚህ በፊት ከሆኑ አራተኛ ይሆናል።
ከዚህ በፊት ባደረግናቸው የትዊተር ዘመቻዎች የአገራችንን ጠላቶች አስደንግጠናቸዋል! መአት ሲያወሩ፤ሲዋሹ፤ የምራቡን ዓለም አስተያየት ለመግዛት ያደረጉትን የክፋት ጥረት ተቋቁመናል።እነሱ ተደራጅተው በያዙት ገንዘብ ረዳት ገዝተው ቢሰለፉም ሊገቱን አልቻሉም።በዓለም፤አቀፍ ደረጃ ተጠራርተን ባጭር ጊዜ ዝግጅት ቀደመናቸው መገኘት ችለናል።በኛ በኩል ገና ያልተጠቀምንበት ትልቅ እምቅ ሃይል አለን። አገር ወዳዱ ሁሉ ይሰለፋል እና ገና ምንኑም አልተነካም።እናጥለቀልቃቸዋለን።

ህወሀት የመርገምት ስም ሆኖ ያገለግል!

እንደ ሕወሀት ያለ ላንድም ቀን ስልጣን ላይ አይደለም  ምድር ገፅ ላይ መቆየት የማይገባው ቡድን 27 አመት በመንግስትነት፣ ሶስት አመት ባሸባሪነት ኖረ። በትቢትና በጥላቻ የናወዘው ይህ የፋሽስት ስግብግቦች ጥርቅም ከተራ የመንደር ሱቅ ቁሳቁሶች እስከ አውሮፕላንና መርከብ ሽያጭ፣ ከካርቶን ቤቶች እስከ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ስርቆሽ ላይ ተጠምዶ ኖረ። አንድ ሀሙስ የቀራቸው መሪዎቹ የሀገሪቱን ወጣቶች ገና የሚወለዱትንም ተከታታይ ትውልዶች ጭምር ራእይ አጨፈገጉ። በነዚህ ድኩማን የሚሊዮን እናቶች እምባ ጅረት ሆኖ ፈሰሰ። ፅንሶች ሳይቀሩ ህፃናት በመላው ሀገሪቱ ተቀጠፉ። ታላቋ አገር ተዋረደች። እምነቶች ረከሱ።

የሶሻል ሚዲያው ግብግብ: ኢትዮጵያን እናፈርሳለን የሚሉትን ዛሬ ዝም ብሎ ማየት እንደማገዝ ይቆጠራል!

ሶሻል ሚዲያ ለአገር ወዳዶችም ሆነ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ለሚሉ ጅሎች ዛሬ የእኩል ጨዋታ ሜዳ ነው።ይህ ጽሁፍ የሶሻል ሚዲያን ጠንቅ እና ጥቅሙንም በጣም ባጭሩ ለመዳሰስ እና ምን ይደረግ ብሎ ለመጠይቅ የቀረበ ጽሁፍ ነው።ለአገር አጥፊም ሆነ በጎ ነገር ሊደረግበት የሚችል ሚሊዮኖች ሰፍረው የሚውሉበት የሚያድሩበትም የህብረተሰባዊ መገናኛ መድረክ ነው።መልክቱ አገር ወዳዶች የውነት ሰራዊት ሆነን መነሳታችን ዛሬ የግድ ነው።ኢትዮጵያን እንወዳታለን እያልን ቆመን ስትፈርስ እንዳናይ ልንሰጋ ጠንክረንም ልንሰራ ይገባናል!